የመስሪያ ቦታዎች ወርሃዊ የኪራይ ተመን

የመስሪያ ቦታዎች የሚገኙበት ቦታ (ሳይት) እና የመሰረተ ልማት አቅርቦታቸውን ታሳቢ በማድረግ በወጣው ደረጃ መሰረት ተፈጻሚ ይደረጋል፡፡

  • በአንደኛ ደረጃ የሚመደቡ መስሪያ ቦታ ውስጥ ገብቶ የሚሰሩ ኢንተርፕራይዞች ዝቅተኛውን የኪራይ መጠን የሚከፍል ሲሆን የኪራይ መጠኑ በካሬ ሜትር ሆኖ ተመኑ እንደሚከተለው ይሆናል፡-

    • ሀ. ለማምረቻ ከጂ+0 እና በላይ ህንፃዎች ወለል የኪራይ መጠን በካሬ ሜትር፡-
      1. የህንፃው ምድር ወለል በካሬ ሜትር በወር ብር 35.00፣
      2. አንድኛ ወለል በካሬ ሜትር በወር ብር 30.00፣
      3. ሁለተኛ ወለል በካሬ ሜትር በወር ብር 26.00፣
      4. ሶስተኛ ወለል በካሬ ሜትር በወር ብር 24.00፣
      5. አራተኛ ወለል በካሬ ሜትር በወር ብር 22.00 ኪራይ ይከፈልበታል፡፡
    • ለ. ለመሸጫና ማሳያ ከጂ+0 እና በላይ ሕንጻዎች ወለል የኪራይ መጠን፡-
      1. የህንፃው ምድር ወለል በካሬ ሜትር በወር ብር 50.00፣
      2. አንደኛ ወለል በካሬ ሜትር በወር ብር 45.00፣
      3. ሁለተኛ ወለል በካሬ ሜትር በወር ብር 40.00፣
      4. ሶስተኛ ወለል በካሬ ሜትር በወር ብር 35.00፣
      5. አራተኛ ወለል በካሬ ሜትር በወር ብር 30.00፣ ኪራይ ይከፈልበታል፡፡
    • ሐ. የወርክ ሾፕ በዘርፍ ወለል የኪራይ መጠን በካሬ ሜትር በወር ብር 20.00 ኪራይ ይከፈልበታል፡፡
    • መ. የሼዶች የኪራይ መጠን በካሬ ሜትር በወር ብር 15.00 ኪራይ ይከፈልበታል፡፡

  • ሁለተኛ ደረጃ የሚመደቡ መስሪያ ቦታ ውስጥ ገብቶ የሚሰሩ ኢንተርፕራይዞች ዝቅተኛውን የኪራይ መጠን የሚከፍል ሲሆን የኪራይ መጠኑ በካሬ ሜትር ሆኖ ተመኑ እንደሚከተለው ይሆናል፡-

    • ሀ. ለማምረቻ ከጂ+0 እና በላይ ህንፃዎች ወለል የኪራይ መጠን በካሬ ሜትር፡-
      1. የህንፃው ምድር ወለል በካሬ ሜትር በወር ብር 30.00፣
      2. አንድኛ ወለል በካሬ ሜትር በወር ብር 25.00፣
      3. ሁለተኛ ወለል በካሬ ሜትር በወር ብር 22.00፣
      4. ሶስተኛ ወለል በካሬ ሜትር በወር ብር 20.00፣
      5. አራተኛ ወለል በካሬ ሜትር በወር ብር 18.00 ኪራይ ይከፈልበታል፡፡
    • ለ. ለመሸጫና ማሳያ ከጂ+0 እና በላይ ሕንጻዎች ወለል የኪራይ መጠን፡-
      1. የህንፃው ምድር ወለል በካሬ ሜትር በወር ብር 45.00፣
      2. አንደኛ ወለል በካሬ ሜትር በወር ብር 40.00፣
      3. ሁለተኛ ወለል በካሬ ሜትር በወር ብር 35.00፣
      4. ሶስተኛ ወለል በካሬ ሜትር በወር ብር 30.00፣
      5. አራተኛ ወለል በካሬ ሜትር በወር ብር 25.00፣ ኪራይ ይከፈልበታል፡፡
    • ሐ. የወርክ ሾፕ በዘርፍ ወለል የኪራይ መጠን በካሬ ሜትር በወር ብር 15.00 ኪራይ ይከፈልበታል፡፡
    • መ. የሼዶች የኪራይ መጠን በካሬ ሜትር በወር ብር 10.00 ኪራይ ይከፈልበታል፡፡

  • የተለጣፊ ሱቅ ፣የኮንቴነር፣ የመደብር፣ የጋራ መኖሪያ ንግድ ሱቆችና አገልግለው ለስራ ዕድል ፈጠራ የሚውሉ አውቶብሶች የኪራይ ክፍያ መጠን ፡-

    • ሀ. አንደኛ ደረጃ መንገድ ላይ ያሉ የተለጣፊ ሱቅና ኮንቴነር የኪራይ ክፍያ መጠን ካሬ ሜትር በወር ብር 120.00፣
    • ለ. ሁለተኛ ደረጃ መንገድ ላይ ያሉ የተለጣፊ ሱቅና ኮንቴነር የኪራይ ክፍያ መጠን በካሬ ሜትር በወር ብር 80.00፣
    • ሐ. የመደብር የኪራይ ክፍያ መጠን በካሬ ሜትር በወር ብር 60.00 ይከፈልበታል፡፡
    • መ. በመንገድ ዳርቻ የሚተከሉ የአውቶብስ ሱቆች የኪራይ ክፍያ መጠን በካሬ ሜትር ወር ብር 50.00 ይሆናል፡፡
    • ሠ. አንደኛ ደረጃ መንገድ ላይ ያሉ የጋራ መኖሪያ ንግድ ሱቆች የኪራይ ክፍያ መጠን በካሬ ሜትር በወር ብር 50.00፡፡
    • ረ. ሁለተኛ ደረጃ መንገድ ላይ ያሉ የጋራ መኖሪያ ንግድ ሱቆች የኪራይ ክፍያ መጠን በካሬ ሜትር በወር ብር 45.00፡፡
  • በሽመና ሥራ በማምረቻ ህንጻ ላይ የተሰማሩ አምራች ኢንተርፕራይዞች ብቻ የመስሪያ ቦታ ዋጋ መጠን ከማምረቻ ህንጻ ትይዩ 30% (ሠላሳ በመቶ) ቅናሽ ይደረግላቸዋል፡፡

  • ቅይጥ የመስሪያ ቦታ ላይ ኪራይ የሚከፈለው በስራ ዘርፉ ይሆናል፡፡

  • የመስሪያ ቦታዎች የኪራይ ተመን እንደ አስፈላጊነቱ የዋጋ ማስተካከያ ሊደረግ ይችላል፡፡

የክፍያ መፈፀሚያ ወቅት የአከፋፈል ሁኔታና የውል ዕድሳት፡-

  1. የመስሪያ ቦታ የወሩ ኪራይ አሰባሰብ የከተማ አስተዳደሩን የገቢ አሰባሰብ ሥርዓት የተከተለ ሆኖ ኢንተርፕራይዙ በገባው ውል መሰረት በካሬ ሜትር በተቀመጠው የኪራይ ተመን መሰረት ለገቢዎች ቢሮ ይከፍላል፡፡
  2. አንድ ኢንተርፕራይዝ የሚጠበቅበትን የኪራይ ክፍያ እስከ ወሩ መጨረሻ ቀን ብቻ ያለቅጣት ይፈጽማል፡፡
  3. አንድ ኢንተርፕራይዝ የሚጠበቅበትን የኪራይ ክፍያ እስከ ወሩ መጨረሻ ቀን መክፈል ያለበትን ጊዜ አሳልፎ ለመክፈል ሲመጣ ለእያንዳንዱ ቀን ለዘገየበት በየወሩ ከሚከፈለዉ ኪራይ ክፍያ መጠን 7% ቅጣት እንዲከፍል ይደረጋል፡፡
  4. ኪራይ ሳይከፍል ከሦስት ወር በላይ የቆየ ኢንተርፕራይዝ ያለምንም ማስጠንቀቂያ ውል ተቋርጦ መስሪያ ቦታውን እንዲያስረክብ በማድረግ ያለበትን እዳ በሕግ አግባብ እንዲከፍል ይደረጋል፡፡
  5. የኪራይ አከፋፈል ሁኔታ ፡-
    • በማምረት ዘርፍ ላይ ለተሰማሩ ኢንተርኘራይዞች የኪራይ ክፍያ በተዋዋሉበት የመስሪያ ቦታ ስፋት መጠን መሰረት በመጀመሪያው ዓመት 25%፣ በሁለተኛው ዓመት 50% በሶስተኛው ዓመት 75%፣ በ4ኛው እና በ5ኛው ዓመት 100% የኪራይ መጠኑን የሚከፍሉ ይሆናል፡፡
    • በንግድና አገልግሎት ዘርፍ ለተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች የኪራይ ክፍያ በተዋዋሉበት የመስሪያ ቦታ ስፋት መጠን መሰረት በመጀመሪያው ዓመት 50% በሁለተኛው ዓመት 75% ከሶስተኛ ዓመት ጀምሮ 100% የኪራይ መጠኑን የሚከፍሉ ይሆናል፡፡
  6. የውል ዕድሳትን በተመለከተ፡-
    • ሀ. በበጀት አመቱ በየትኛውም ወር የመስሪያ ቦታ ተጠቃሚ የሆነ ኢንተርፕራይዝ የኪራይ ውሉን በአዲሱ በጀት አመት መጀመሪያ ከሐምሌ 1 እስከ መስከረም 30 ባለው ጊዜ ውስጥ ውሉን ማደስ አለበት፡፡
    • ለ. በተሰጠው የውል ማደሻ ጊዜ ያላደሰ ኢንተርፕራይዝ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት በማስጠንቀቂያው መሠረት ውል ካላደሰ በገዛ ፈቃዱ የመስሪያ ቦታውን እንዳልፈለገ ተቆጥሮ ውል ይቋረጣል፡፡
  7. ውል ለማሳደስ ኢንተርፕራይዞች ማሟላት ያለባቸው መስፈርት፤
    • ሀ. የወርሃዊ ክፍያ የዓመቱን የከፈሉበትን ህጋዊ ደረሰኝ መቅረብ አለበት፤
    • ለ. በእጃቸው ያለውን ለመጨረሻ ጊዜ የተዋዋሉበትን የውል ሰነድ ይዘው መቅረብ አለባቸው፣
    • ሐ. የግቢ ግዴታ ስለመወጣቱ የሚያሳይ ማስረጃ፣
    • መ. የኢንተርፕራይዙ ስራ አስኪያጅ ወይም የማህበሩ አባል የሆነ ተወካይ መቅረብ አለበት፡፡