አዲስ የመስሪያ ቦታ ጥያቄ ለሚያቀርቡ የጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ሟሟላት የሚገባቸው ጉዳዮች፣

  • የሚመለመሉ ኢንተርፕራይዞች ኤጀንሲው ከሚያስተዳድረው የመሥሪያ የቦታ መጠንና የዘርፍ አይነት ጋር የተመጣጠነ ሲሆን፣

  • ከቢሮ እና አስከ ወረዳ ባሉ የቢሮ መዋቅር ተመልምለው ወደ ኤጀንሲው የሚመጡ ኢንተርፕራይዞች የመስሪያ ቦታ ድጋፍ እንዲደረግላቸው የተወሰነበት ቃለ ጉባኤ ከነአስፈላጊ የአደረጃጀት ሰነዶች ጋር መቅረብ ሲችል፣

  • የጥቃቅን ወይም አነስተኛ ወይም የመካከለኛ ኢንትርፕራይዝ የዕድገት ደረጃ ማረጋገጫ ሲያቀርብ፣

  • ለአዲስ ኢንተርፕራይዝ አዋጭ ቢዝነስ ፕላን ሲያቀርብ፣

  • የከተማ የነዋሪነት መታወቂያ፣

ለመሸጫና ማምረቻ ዘርፍ አገልግሎት የሚውል ህንፃ ላይ የመስሪያ ቦታ አሰጣጥን በተመለከተ፡-

  • ለህንፃው ደህንነት ሲባል በሚቀርቡት የማምረቻ መሳሪያዎች እና ዕቃዎች ክብደትና የስራው ባህሪ የቦታ ምደባው በኤጀንሲው የሚወሰን ሆኖ በአንቀጽ 8(1-4) የተጠቀሱት ምርትና አገልግሎቶች የሚገቡ ይሆናል፡፡

  • በመሸጫ ህንጻ ላይ ለኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ፣ ለኢንተርኔትና ኮምፒውተር ጥገና አገልግሎቶች 3ኛ ወለል ላይ የሚሰጥ ሲሆን የሚከተሉት የስራ መስኮች በምድር እና በአንደኛ ወለል የሚደለደሉ ይሆናል፡፡

    • በዘርፉ ስራ ላይ የተሰማሩ አካል ጉዳተኞች እና መውጣትና መውረድ እንደማይችሉ በህክምና ማስረጃ የተረጋገጠላቸው ህሙማን፤
    • የአትክልትና ፍራፍሬ፣ ካፌና ሬስቶራንትና የእንስሳት ተዋጽኦ፤
    • የእንጨትና ብረታ ብረት ውጤቶችና የኮንስትራክሽን ውጤቶች
    • ሌሎች ተጠቃሚዎች በየትኛውም ቦታ ሊመደቡ ይችላሉ፡፡

  • የገበያ ማዕከል (ኢንፖሪየም) ማሳያን በተመለከተ በቀጣይ በሚገነቡ ማዕከላት ኤጅንሲው በሚያወጣው የቦታ አጠቃቀም ማሰፈጸሚያ ሰነድ መሰረት ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

የመስሪያ ቦታ ቅድሚያ የሚሰጣቸው ኢንተርፕራይዞች ወይም የህብረተሰብ ክፍሎች፡-

  1. በአነስተኛና መካከለኛ ዕድገት ደረጃ በስራ ላይ ያሉና ለወጣቶችና ሴቶች የስራ ዕድል መፍጠር እየቻሉ፤ ከዚህ በፊት የመስሪያ ቦታ ተጠቃሚ ያልሆኑ እና የመስሪያ ቦታ ማነቆ የሆነባቸው ነባር አምራች ኢንተርፕራይዞች፤
  2. ከዩኒቨርሲቲ፣ ከኮሌጅ እና ከቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት ተመርቆ በልዩ ፈጠራና ተክኖሎጂ ለአምራች ዘርፍ ምርታማነት አስተዋፆ ለማድረግ በግልም ሆነ ተደራጅቶ ለሚመጡ ወጣቶች፣
  3. ችግር ፈቺ ልዩ የስራ ፈጠራ ባለቤት የሆኑ ከአእምሯዊ ንብረት ተቋም ዕውቅና የምስክር ወረቀት ያላቸው፤
  4. ለአምራች፣ለኮንስትራክሽን ግባዓት ማምረትና ለግብርና ሥራዎች እንዲም የከበረ ማዕድን ሥራዎች ዘርፍ የሚፈጥሩት የስራ ዕድልና ለኢኮኖሚ በሚያበረክቱት አስተዋፆ ከግምት በማስገባት፣
  5. ለአካል ጉዳተኞች እንደየ ጉዳታቸው መጠን፤
  6. የሚሰሩበት የኤጀንሲው መስሪያ ቦታ በልማት ምክንያት የፈረሰና ግዴታቸውን የተወጡ መሆናቸውን ሲረጋገጥ፤
  7. በአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዝ የተደራጁ ሴቶች ፣
  8. በልዩና ወቅታዊ ሁኔታዎች የከተማ አስተዳደሩ የበላይ አካል ውሳኔ መሰረት የመስሪያ ቦታ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የሚወሰንላቸው ዜጎች፤
  9. በአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ዕድገት ደረጃ ሆኖ ከውጭ የሚገባ ምርትን ለመተካት የሚያመርቱ አምራቾች እና የውጭ ምንዛሬ የሚያስገኙትን ጨምሮ ከላይ የተጠቀሱት ኢንተርፕራይዞች ወይም የህብረተሰብ ክፍሎች መስሪያ ቦታ በምደባ ሊሰጣቸው ይችላል፡፡
  10. ከላይ የተጠቀሱት እንደተጠበቀ ሆኖ ሌሎች የግልና የተደራጁ ኢንተርፕራይዞች ኤጀንሲው በሚያዘጋጀው መስፈርት መሰረት መስሪያ ቦታ በውድድር የሚሰጣቸው ሆነው በውድድሩ ተመሳሳይ ውጤት የሚያመጡት ኢንተርፕራይዞችን እንደየሁኔታው በዕጣ ተለይቶ የመስሪያ ቦታ የሚሰጣቸው ይሆናል፡፡