በመስሪያ ቦታዎች ለሚገቡ ኢንተርፕራይዞች የሚሰጥ የቦታ ስፋት መጠን፡-

  • ከቢሮው ተደራጅተው ለሚመጡ ኢንተርፕራይዞች ወይም በግላቸው ተከራይተው በማምረት ዘርፍ የሚሰሩ አምራቾች የሚፈጥሩት የስራ ዕድልና ከቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ጋር በትስስር ለመስራት ዝግጁ ለሆኑት በመመልመያ መስፈርት መሰረት ተለይተው መሰሪያ ቦታ ይሰጣቸዋል፡፡

  • የሚሰጠው ቦታ መጠን የኢንተርፕራይዞችን የእድገት ደረጃ መሰረት ከሚይዙት የሰው ሃይል ብዛት አኳያ ታሳቢ ተደርጎ ኤጀንሲው በሚኖረው የቦታ ስፋት ላይ የተመሰረተ ይሆናል፡፡

  • ከአእምሯዊ ንብረት ተቋም ዕውቅና ተሰጥቷአቸው ችግር ፈቺ ልዩ የፈጠራ ስራ ይዘው ለሚቀርቡ ኢንተርፕራይዞች በሚያቀርቡት የንግድ ስራ ዕቅድ፤የዕውቀት ሽግግር፤የሚፈጥሩት የስራ ዕድልና ለአምራች ዘርፍ በሚያበረክቱት ምርታማነት መሠረት መሰረት በማድረግ መስሪያ ቦታ ሊሰጣቸው ይችላል፡፡

  • በማምረቻ ቦታዎች ውስጥ ለሚገቡ አምራች ኢንተርፕራይዞች የሚሰጣቸው የቦታ መጠን፡

    • ለልብስ ስፌት፣ ለሹራብ ስራ፣ ለጥልፍ ሥራ እና የቆዳ ውጤቶች 4 ካሬ ሜትር በሰው ሆኖ ለጥቃቅን ከ4 ካ/ሜ እስከ 20 ካ/ሜ፣ ለአነስተኛ አምራች ከ24 ካ/ሜ እስከ 120 ካ/ሜ፣ ለመካከለኛ ከ125 ካ/ሜ እስከ 400 ካ/ሜ ይሆናል፡፡
    • ለሸማ ሥራ 6 ካሬ ሜትር በሰው ሆኖ ለጥቃቅን ከ6-30 ካ/ሜ፣ ለአነስተኛ ከ36 እስከ 180 ካ/ሜ ለመካከለኛ ከ186 እስከ 340 ካ/ሜ ይሆናል ፡፡
    • ለካፌ እና ሬስቶራንት ለጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች 32 ካሬ ሜትር ለ5ና ከዚያ በላይ ሆነው ለተደራጁ ኢንትርፕራይዞች የሚሰጥ ይሆናል፡፡
    • ለውበት ሳሎን፣ ለአይሲቲ (ICT) እና ለኢንተርኔትና ኮምፒውተር ጥገና አገልግሎቶች ለጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች 32 ካሬ ሜትር ለ5ና ከዚያ በላይ ሆነው ለተደራጁ ኢንትርፕራይዞች የሚሰጥ ይሆናል፡፡
    • ለእንጨትና ብረታ ብረት፣ ቀለምና ቫርኒሽ፣ ሚስማር ማምረቻ፣ ለብሎኬት፤ የድንጋይ ማስዋብ እና ሌሎች የኮንስትራክሽን ግብዓት ማምረቻ፣ ለመልሶ መጠቀም፣የኬሚካል ውጤቶች፣ ሳሙና እና ዲተርጀንት፣ የከበሩ ማዕድናትና ጌጣጌጥ፣ ለህትመት ስራዎች ለጥቃቅን እና ለአነስተኛ እስከ 120 ካ/ሜ ለመካከለኛ እስከ 480 ካ/ሜ ይሰጣል፡፡
    • ለፕሪካስት ምርት ማምረት 5 እና ከዛ በላይ አባላት ላሉት 240 ካ/ሜ ይሰጣል፡፡
    • የደረቅ ምግብና የባልትና ውጤቶች፣ ለአግሮ ፕሮሰሲንግ ስራዎች፣ ከረሜላ ማምረት ለጥቃቅን እስከ 60 ካ/ሜ፣ ለአነስተኛ እስከ 120 ካ/ሜ፣ለመካከለኛ እስከ 240 ካ/ሜ ይሰጣል፡፡
    • የጂ+2 የምግብ ማቀነባበሪያ (የአግሮ ፕሮሰሲንግ) ቦታ አሰጣጥን በተመለከተ ለመካከለኛ ኢንተርፕራይዝ እስከ 400 ካ.ሜ ይሰጣል፡፡
    • ለባህላዊ ዕደ-ጥበብና ጌጣጌጥ ሥራዎች ወይም የቀንድና የሸክላ ስራ፤ ቀርከሀ፤ ስጋጃ፤ የከበሩ ድንጋዮችና የብር፣ የነሐስ ጌጣጌጥ ስራ እና የአሻንጉሊት ስራዎች ለጥቃቅን፣ አነስተኛ መካከለኛ 120 ካ/ሜ ይሰጣል፡፡
    • ለወተት ከብት እርባታና ለከብት ማድለብ ለጥቃቅን እስከ 120 ካ/ሜ፣ ለአነስተኛና መካከለኛ እስከ 240 ካ/ሜ ይሰጣል፡፡
    • ለበግና ፍየል ማድለብና እርባታ፣ ዶሮ እርባታ፣ እንጉዳይ ማምረትና መኖ ማቀነባበሪያ ለጥቃቅን እና አነስተኛ ደረጃ ላላቸው 120 ካሬ ሜትር ለ5 እና ከዚያ በላይ አባል ያለው ኢንተርፕራይዝ የሚሰጥ ሆኖ ለመካከለኛ እስከ 240 ካሬ ሜትር ይሰጣል፡፡

  • በመሸጫ ቦታዎች ውስጥ ለሚገቡ ኢንተርፕራይዞች የሚሰጣቸው የቦታ መጠን፡-

    • የመጀመሪያ ወለልና 1ኛ ፎቅ ላይ ለብረታብረት ኢንጂነሪንግና እንጨት ውጤቶች ለጥቃቅን እስከ 32 ካ/ሜ፣ ለአነስተኛ እና ለመካከለኛ እስከ 100 ካ/ሜ ቦታ የሚሰጥ ይሆናል፡፡
    • ከብረታብረት ኢንጂነሪንግና እንጨት ውጤቶች ውጭ ለሆኑ ኢንተርፕራይዞች የሚሰጥ የቦታ መጠን ለጥቃቅን እስከ 12ካ/ሜ፣ ለአነስተኛ ኢንዱስትሪ ከ16 ካ/ሜ እስከ 48 ካ/ሜ ለመካከለኛ ኢንዱስትሪ ከ32 ካ/ሜ እስከ 68 ካ/ሜ ይሆናል፡፡
  • የጋራ መጠቀሚያው በእያንዳንዱ ኢንተርፕራይዝ የኪራይ ዉል ላይ ተካቶ በሚወጣው ማስፈጸሚ ማኗል መሰረት ይከፈላል፡፡
  • በዚህ መመሪያ ከተጠቀሱት ምርቶችና አገልግሎቶች ውጪ ጥያቄ ሲቀርብ እንደ ስራው ባህሪ የቦታ መጠን በኤጀንሲው በኩል በሚሰጠው ውሳኔ መሰረት የሚስተናገዱ ይሆናል፡፡
  • አዋጁ በሰጠው ሥልጣን መሰረት አጄንሲው የሚያስተዳድራቸው መስሪያ ቦታዎች የተለያየ ገፅታ ያላቸው በመሆኑ እና እኩል ተደራሽ ባለመሆናቸው ለዋናው መንገድ ባላቸው ቅርበት፣ ከዋና ዋና የገበያ ቦታዎች ያላቸውን ርቀት እና የተሟላላቸው መሰረት ልማት ሁኔታን በመመዘን በደረጃ ተከፍሏል፡፡

    • ለዋናው መንገድ እና ለዋና ዋና የገበያ ቦታዎች የቅርብ ርቀት ውስጥ የሚገኙ እንዲሁም ሁሉም መሰረተ ልማት የተሟላላቸው በአንደኛ ደረጃ ይመደባሉ፡፡
    • ከዋናው መንገድ፣ ከዋና ዋና የገበያ ቦታዎች ርቀት ላይ የሚገኙ እና በከፊል መሰረተ ልማት የተሟላላቸው እንዲሁም መንገድ ዳር ሆነው መሰረተ ልማት ያልተሟላላቸው በሁለተኛ ደረጀ ይመደባሉ፡፡
  • በማምረቻ ህንጻ፣ ወርክ ሾፕ፣ በመሸጫ ህንጻና ሼድ የሚሰጠው የቦታ ስፋት እንደተጠበቀ ሆኖ የመስሪያ ቦታ ማስፋፊያ ሲያቀርቡ ኢንተርፕራይዞች እንደየ እድገት ደረጃቸው የሚከተሉት ቅድመ ሁኔታ ሲያሟሉ ሊስተናገዱ ይችላሉ፤

    • የተዘጋጀው የንግድ ስራ እቅድ የሚፈጥረው ተጨማሪ የስራ ዕድል፣የዕቅዱ አዋጪነቱና ተግባራዊነቱ በቢሮ እና በክፍለ-ከተማ ተረጋግጦ ሲቀርብ፣
    • በገቢ ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተረጋገጠ የአንድ ዓመት የቋሚ ሰራተኛ ደመወዝ መክፈያ ፔሮል መኖሩ ሲረጋገጥ፤
    • ከሚመለከተው ተቋም የሚያስገባው አዲስ የመስሪያ ማሽን የሚይዘው የቦታ ስፋት መጠን የሚገልጽ ማስረጃ ሲቀርብ፤
    • የታደሰ የዕድገት ደረጃ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል ከሆነ፣
    • የመስሪያ ቦታ ማስፋፊያ አስፈላጊነት ውሳኔ በቢሮ ወይም በክፍለ ከተማ በሚገኙ ጽ/ቤቶች ተረጋግጦ ሲቀርብ፣
    • የያዘው መስሪያ ቦታ ከ4 ዓመት በታች የተጠቀመ መሆኑ ሲረጋገጥ፡፡
    • የአከባቢ ጥበቃ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት እንዲያቀርቡ የሚጠበቁ የስራ ዘርፎች ምርቶች፤ሳሙናና ዲተርጀንት ማምረት፤ከረሜላ ማምረት፤ቀለም እና ቫርኒሽ ማምረት፤የእንጨት ስ ራዎች፤ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ስራዎች፤ የቆዳ ውጤት፤ የከበሩ ማዕድናትና ጌጣጌጥ ሥራና የኬሚካል ምርቶች ስራዎች፤የከተማ ግብርና ወረቀት መልሶ መጠቀም፣ፕላስቲክ፣ ህትመትና የወረቀት ስራዎች፣ አግሮ ፕሮሰሲንግና ደረቅ ምግብ እንዲሁም የአካባቢ ጥበቃ ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል ተብለው ሲታመን ለኤጀንሲው ቀርቦ ሲጸድቅ አሟልቶ ማቅረብ የሚችሉ ናቸው፡፡

ለበለጠ መረጃ ይህን መመሪያ ቁ109/2014 ያንብቡ