በከተማችንም ሆነ እንደ ክ/ከተማችን የፐቭሊክ ሰርቪስ እና የሰው ሃብት ልማት ጽ/ቤት ዘርፍ ህብረተሰቡ የሚያነሳቸውን የልማት እና የመልካም አስተደደር ጥያቄዎችን ምላሽ እንዲያገኙ የሪፎርም ስራዎችን በማስተባበር የአገልግሎት አስጣጥ ሂደቱ ግልጽ፤ፈጣን ፍትሃዊና ተደራሽ ለማድረግ በተካሄዱ እንቅስቃሴዎች የማይናቅ ውጤት ሊመዘገብ ችሏል፡፡ ይሁንና ከነዋሪው ፍላጎትና መምጣት ካለበት ለውጥ አንጻር ሲታይ አሁንም በርካታ ከፍተቶች ይስተዋላሉ፡፡
በመሆኑም ያሉትን ክፍተቶች በመሙላት ልማትና መልካም አስተዳደር በማረጋገጥ የተገልጋዩን ህዝብ እርካታ ለማረጋገጥ የለውጥ ስራ አመራር መሳሪያዎች የሆኑትን ቢፒአርና ቢኤሲሲ ቅንጅታዊ ትገባራን እውን በማድረግ ለውጡን ይበልጥ ቀጣይነት እንዲኖረው ለማስቻል የጉዳዩ ባለቤት የሆነው ህዝብ የነቃ ተሳትፎ ኖሮት የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ማደረግ አሰፈላጊ ነው፡፡
ይህ የሚሆነው ደግሞ የህዝቡን ቀጥተኛ ተሳታፊነት እና ተጠቃሚነት ሊያራጋግጥ የሚያስችል የዜጎች የስምምነት ቻርተር በማዘጋጀት ተገልጋዩ ህዝብ በአገልግሎት ሰጪ ተቋማት የሚሰጡ አግልግሎቶችን በግልጽ እንዲያውቃቸው መብቱንና ግዴታውን አውቆ በመልካም አስተዳደርና በአገልገሎት አሰጣጥ ችግሮች አፈታት ላይ እንደዚሁም ልማትን በማፋጠን በኩል የራሱን ድርሻ እንዲወጣ ማድረግና ተገልጋዮች ወደ ጽ/ቤቱ አገልግሎት ለማግኘት ሲመጡ የሚሰጣቸውን የአገልግሎት ዓይነትና ጥራት፤ የሚወስደውን ጊዜ አገልግሎቱን ለማግኘት የሚያስፈልጋቸው ወጪና እንዲሁም በእነርሱ በኩል ማሟላት የሚገባቸውን ቅድመ ሁኔታዎችን ያመላከተ የተገልጋዮች ቻርተር ማዘጋጀት አስፈላጊ መሆኑን በማመን እንደሚከተለው ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡
የዜጎች ስምምነት ሰነድ ዓላማ
-
በክፍለ ከተማችን የሚሰጡ አገልግሎቶችን ለህብረተሰቡ ተደራሽ፤ ፍትሃዊና ተገልጋይ ተኮር ለማድረግ ብሎም የተጀመሩ የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን አጠናክሮ በማስቀጠል የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ዜጎች ለልማቱ ባበረከቱት ልክ ማግኘት የሚገባቸዉን ጥቅም በአግባቡ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማድረግ
-
ግልፀኝነትና ተጠያቂነት ያለው የአሰራር ስርአት ለማስፈን፣
- አገልግሎት አሰጣጡ በተጠናው ስታንዳድ መሰረት እንዲሰጥ ለማድረግ፣
- በስታንዳርዱ መሰረት አገልግሎት የማይሰጡ አካላት ላይ ተጠያቂነትን በማስፈን የመልካም አስተዳደር ቸግሮችን መፍታት ናቸው፡፡
- ሁሉም ተገልጋዮች በስራ ኢንተርፕራይዝ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የባለቤትነት ስሜት ተሰምቷቸው አስተያየት ጥቆማና ማናቸውንም ግብዓት በነጻነት የሚሰጡበትን ሁኔታ ለማመቻቸትና ለመተግበር ነው፡፡
ስትራቴጂያዊ የትኩረት መስኮች እና ውጤታቸው
-
የሰው ሃብት ብቃትና አመራር ልህቀት
በስነ ምግባር የታነጸ፣ ብቁና ተወዳዳሪ የሰው ሃይል /ፈጻሚና አመራር/ ይፈጠራል፡፡
ክፍተትን መሰረት ያደረገ የአመራርና ባለሙያ ስልጠና በመስጠት አቅም ይጎለብታል፤
በምልመላ፣ በመረጣና በስምሪት ሂደቱ ምጣኔው የተስተካከለ የሰው ኃብት አመራር ስርዓት ይፈጠራል፡፡
ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት አሰጣጥ ይረጋገጣል፡፡
-
የአደረጃጀት፣ የአሰራርና የአገልግሎት አሰጣጥ ልህቀት
ሪፎርም ፕሮግራሞች በሁለም አስተዳደር እርከኖች በተሟላ ሁኔታ እንዲተገበሩና በማስቻል ለውጡ ተቋማዊ ባህል ይሆናል፡
ወቅቱን ያማከለና ስራውን ሊይዝ የሚችል ብቁ መዋቅራዊ አደረጃጀት ይፈጠራል፡፡
ከተቋማት ተጨባጭ ሁኔታ የተቃኘ ዘመናዊ የአሰራር ስርዓት ይዘረጋል፡፡
ደረጃውን የጠበቀና ዘመናዊ የስልጠና ፋሲሊቲ አገልግሎት በመስጠት የስልጠና ውጤታማነት ከፍ እንዲል ይደረጋል፤
የበለጠ ተዓማኒ፣ ቀልጣፋ፣ ተደራሽ እና ውጤታማ አገልግሎት አሰጣጥ ይረጋገጣል፡፡
የተቋሙ ስልጣንና ተግባራት
የተገልጋዮች መብት
- ስለ አገልግሎቶች የተሟላ መረጃ የማግኘት፣ የመጠቀምና የሚጠይቀውን ወጭ የማወቅ ብት፣
- ተገቢውን አገልግሎት ሳያገኝ ሲቀር ማስተካከያ የመጠየቅ መብት፣
- ሁሉም አገልግሎቱን በእኩልነትና በፍትሐዊነት የማግኘትና የመጠቀም መብት አላቸው፤
- በአገልግሎት አሰጣጣችን ላይ ጥያቄ የመጠየቅ እና ማብራሪያ የማግኘት መብት፡፡ ፤
- ተገልጋዮች አገልግሎቱን ሙሉ ወይም በከፊል ለማግኘት ሲመጡ ማሟላት ያላባቸውን ሁኔታዎች በቅድሚያ የማወቅ መብት አላቸው፡፡፤
- የምክር አገልግሎት የማግኘት መብት፣
- በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ አስተያት/ቅሬታ የማቅረብ እና ላቀረቡት ጥያቄ ፍታሃዊ እንዲሁም ወቅታዊና በቂ መልስ የማግኘት መብት፣
- ልዩ ትኩረት ለሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎች በተለያየ መልኩ የመስተናገድና አግልገሎት የማግኘት መብት፤
- በጽ/ቤቱ ዕቅድ፣ ሪፖርትና ግብረ መልስ ላይ መሳተፍና አስተዋጽዖ የማድረግ፡፡ ፤
- ፍትሃዊና አድሎ የሌለበት አገልግሎት የማግኘት መብት፤
የተገልጋዮች ግዴታዎች
- የአገልግሎት ሰጪ ተቋምን ሕጎችን የአሰራር መመሪያዎችን መከተል
- ትክክለኛ መረጃዎችን የማቅረብ ግዴታ
- የአገልግሎት ቅድመ ሁኔታዎችን የማሟላትና የማቅረብ ግዴታ
- የጽ/ቤታችን ህግና ሥርዓት የማክበር ግዴታ