
በ2022 ዓ.ም ዘመናዊ የመስሪያ ቦታ በማልማት አቅርቦቱን በማፋጠንና አስተዳደራዊ አሰራሩን በማዘመን በዘርፉ የተሰማሩ ኢንተርፕራዞች እና ኢንዱስትሪዎች ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ተረጋግጦ ማየት ፡፡
የዘርፉን እድገት ያማከለ ተጨባጭ ጥናት ላይ የተመሰረተ እና መሰረተ ልማት የተሟላላት ደረጃውን የጠበቀ የመስሪያ ቦታ ገንብቶ በማስተላለፍ እና ፈጣን አገልግሎትን መሰረት ያደረገ ዘመናዊ አስተዳደርን በመዘርጋት የኢንተርፕራዞች እና አምራች ኢንዱስትሪዎችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ነው፡፡
በሀገር ደረጃ የተጀመረዉን ሪፎርም በማስረጽ የአገልግሎት አሰጠጡን ተደራሽ፣ ግልጽና ወጪ ቆጣቢ በማድረግ የጽ/ቤቱን ራዕይ እና ተልዕኮ ለማሳካት ዘመን የወለዳቸውን የቴክኖሎጂ ዉጤቶች አቀናጅቶ ውጤታማ ስራ ለማከናወን እየተደረገ ያለዉ እንቅስቃሴ ከመቼውም ጊዜ በላይ የተሻለ ነዉ፡፡
የስራ አካባቢን ሳቢ ፣ ፅዱና ምቹ ከማድረግ ጋር ተያይዞም በጽ/ቤቱ ለአገልግሎት አሰጣጥ ከፍተኛ ችግር ፈጥሮ የነበረውን የተከማቸ ፋይል በማንሳት ፤ የካይዘንን ፍልስፍና ተግባራዊ በማድረግ የፈጻሚውን አቀማመጥ በማስተካከል ችግር የነበረባቸውን የፈጻሚ ወንበሮች በመለወጥና በማደስ ቢሮውን የማሳመር ተሰርቷል፡፡
Visit our Web App
ዉድ ደንበኞቻችን የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታትና የለውጥ ሥራዎችን ቀጣይነት ለማረጋገጥ የተቋሙን አገልግሎት አሰጣጥ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ በብቃቱና እና በሥነ-ምግባሩ የተመሰገነ የሰው ኃይል እንዲመራ በማድረግ አገልግሎቶቻችንን እናሻሽል ዘንድ የእርሶ አስተያየት አስፈላጊ ነዉና እባክዎ የአገልግሎት እርካታ አስተያየት መስጫ ሳጥንን በመጫን አስተያየትዎን ይስጡን።
በተጨማሪም
ስለሆነም ጽ/ቤቱ የሚሰጠው አገልግሎት ክፍለ ከተማውን የመስሪያ ቦታ የማልማት አቅምና የተገልጋይ ፍላጎትን መሰረት በማድረግ የመስሪያ ቦታ አቅርቦት በፍትሀዊነት ይበልጥ ተደራሽ ለማድረግ እና ኢኮኖሚዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚሰጡ አገልግሎት አይነቶች፣ አገልግሎቱ የሚሰጥበት ስታንዳርድ፣ አገልግሎቱ የሚሰጥበትን ቦታ እና ከተገልጋይ የሚጠበቁ ቅድመ ሁኔታዎችን በግልጽ በዝርዝር ማስቀመጥ አስፈላጊ በመሆኑ በዘመናዊ መልክ ተደራጅቶ ቀርቦላችኋል፡፡
If you have any question please do not hesitate to call or contact us. Our Address is
Ayat round about near allmart Supper market, Lemi Kura Subcity Administration Buildind 2nd Floor, Addis Ababa, Ethiopia.
Phone: +251929339403
Email: 2022
© 2024 Lemi Kura Working Premises D/A/ Office. Designed by Markos MG 0912689710.